አምስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ስነ-ህዝብና ጤና ጥናት የመጀመሪያ ደርጃ ሪፖርት ውጤት ለተጠቃሚዎች ይፋ ተደረገ

t8a8162

ጥር 16/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2016 ዓ.ም ያካሄደውን አምስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ስነ-ህዝብና ጤና ጥናት የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ውጤት የፕላንና ልማት ሚኒስትር ፣ የጤና ሚኒስትር፣ የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስትር፣ ዓለም አቀፍና ሀገር አቀፍ አጋር ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ለተጠቃሚዎች ይፋ አደረገ።

t8a8107

በስርጭት መድረኩ ላይ የተገኙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በብዙ ችግሮች ውስጥ አልፎ ለሀገራችን የጤና ዘርፍ ቁልፍ አመላካች የሆነውን የዚህ ጥናት ውጤት ለተጠቃሚዎች ይፋ ማድረግ ላይ በማድረሱ ምስጋናቸውን አቅርበው በጤናው ዘርፉ ለሚካሄዱት የሪፎርም አጀንዳዎችን ዕውን ለማድረግ ከጥናቱ የሚገኙ መረጃዎች ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳላቸው ገልፀዋል።

t8a8145

ተቋማቸው ከሚሰራቸው የእናቶች፣ ህፃናትና ከስርዓተ ፆታ ጋር የተያያዙ ስራዎች ከጥናቱ የሚገኙ መረጃዎችና ለእናቶችና ለህፃናት ምቹ ሀገር እንድትኖረን መንግስት ለሚሰራቸው የዘርፉ ዋና ዋና ተግባራቶች ቁልፍ ፋይዳ እንዳላቸው የሴቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ኤርጎጌ ተስፋዬ ተናግረዋል።

ስርጭቱን በይፋ ያስጀመሩት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ ስራው እንዲክሳካ መንግስት መረጃን እንደአንድ ቁልፍ ልማት በመመልከት ጥናቱ ተጀምሮ እስከሚጠናቀቅ ድረስ አስፈላጊውን ድጋፍ ማድረጉን ገልፀው፤ ይህ ስራ ከተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ውጪ እውን ስለማይሆን የተቋሙ አመራርና ሰራተኞች ስራው እንዲሳካ ላደርጉት ትጋትና ጥረት ምስጋናቸው አቅርበው ከዛሬው ዕለት ጀምሮ የመጀመሪያ ደረጃ ሪፖርት ውጤት ለተጠቃሚዎች መሰራጨቱን ይፋ አድርገዋል።

t8a8082

መረጃው ቁጥር ብቻ ሳይሆን የህዝባችን ድምፅ ነው ያሉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በዚህ ስራ ውስጥ ለተሳተፉ አመራር፣ ሰራተኞችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ምስጋናቸውን ገልፀው የዛሬው መድረክ ከመረጃ ስርጭት ባለፈ ጠንካራ የሆነ አጋርነት የምንፈጥርበት መድረክ ነው ሲሉ ገልጸዋል።

t8a8208

ጥናቱ በዋናነት በጨቅላ ህፃናትና እናቶች ጤና ላይ አመላካች የሆኑ የወሊድ ምጣኔናና የቤተሰብ እቅድ አጠቃቀም፣ ስለክትባት አወሳሰድ፣ እናቶች ከወሊድ በፊትና በኋላ የሚደረግላቸው የጤና እንክብካቤ፣ ኤች አይ ቪ ስርጭት፣ የህፃናት መቀንጨርና አመጋገብን የሚያሳዩ አመላካቾች እንደሚገኙበት ከቀረበው ገለፃ ለመረዳት ተችሏል።

t8a8213
t8a8214
t8a8228
t8a8256