
ነሐሴ 1/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣
በ2018ዓ.ም በሚያካሄደው የግብርና ናሙና ጥናትና ላይ ከብሔራዊ ቲክኒካል ኮሚቴ ጋር ውይይት ተደረገ።
የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ዓመታዊ የግብርና ናሙና ጥናት የግብርና ቆጠራ በተካሄደበት ማግስት መካሄዱ በቆጠራው የተገኙ ግብዓቶችን በማካተት ጥራት ያለው የግብርና ናሙና ጥናት ለማከናወን እንደሚያግዝ ገልፀው፤የውይይት መድረኩ የተዘጋጀው ከባለድርሻ አካላት ጋር በመወያየት የሚነሱ አስተያየቶችን እንደግብዓት ለመጠቀም ታስቦ መሆኑን ገልፀዋል።

በመድረኩ ከፕላንና ልማት ሚኒስቴር፣ ከግብርና ሚኒስቴርና ሌሎች ተቋማት የተውጣጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን ለጥናቱ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦች ተነስተዋል።

