
የሲዳማ ብሔራዊ ክልል መንግስት ርዕሰ መስተዳደር አቶ ደስታ ሌዳሞ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በስታቲስቲክስ ልማት ዕቅድ ፕሮግራም እያከናወናቸው በሚገኙ ቆጠራዎችና ጥናቶች ላይ ለስራው መሳካት በሲዳማ ክልል ከሚገኘው የሀዋሳ ስታቲስቲክስ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ጋር በቅርበት በመደገፍ ለሀገራዊ ስታቲስቲክስ ቆጠራዎች እና ጥናቶች መሳካት ምቹ ሁኔታዎች እንደሚፈጥሩ ገልፀዋል:: በ2017ዓ.ም በክልሉ ውስጥ የተከናወኑ ተግባራትም ውጤታማ እንደነበሩ እና የክልሉ ድጋፍ አዎንታዊ ድርሻ እንደነበረው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አመራሮች ገልፀዋል:: ለቀጣይም ይሄው ድጋፍ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አመራሩ ጠይቋል::