
ጥር 12 /2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ
ሁለተኛ ምዕራፍ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች የሚሰጠውን ስልጠና በየስልጠና ማዕከላቱ ተገኝተው ለሚደግፉ ባለሙያዎች የስራ ስምሪት ተሰጠ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በመላ ሀገሪቱ በ55 የስልጠና ማዕከላት ለሚሰጠው የሁለተኛ ምዕራፍ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመረጃ ሰብሳቢዎች፣ የስታቲስቲሺያኖች እና የተቆጣጣሪዎች ስልጠና ለመደገፍ የተመደባችሁት ባለሙያዎች በጊዜ በየስልጠና ማዕከላቱ በመገኘት የስልጠና ቦታዎቹ ለሰልጣኞች አስቻይና ምቹ መሆናቸውን በማረጋገጥ በመስክ የሚፈለገውን ጥራቱ የተጠበቀ መረጃ የሚሰበስቡ ብቁ ባለሙያዎች ለማፍራት የሚሰጠው ስልጠና በተሟላ መልኩ በስኬት እንዲጠናቀቅ ከሌሎቹ ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ሁሉ ድጋፍ ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

ስልጠናው በ55ቱ የስልጠና ማዕከላት ከጥር 14-23/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።