ታህሳስ 27/2018 ዓ.ም አዳማ፣
ከተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና ከ26ቱ ቅ/ጽ/ቤቶች ለተወጣጡት ከፍተኛ ባለሙያዎች ላለፉት 10 ቀናት በአዳማ ከተማ ሲሰጥ የቆየው የምዕራፍ ሁለት የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የቅድመ አሰልጠኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።

በስልጠናው ማጠቃለያ መድረክ ላይ የተገኙት የተቋሙ የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ዶ/ር ሜሮን ክፈለው ስልጠናው በታቀደው መሠረት በከፍተኛ ትጋትና ዲስፕሊን ተከታትለው በማጠናቀቃቸው ለሰልጠኞቹ ምስጋና አቅርበው በቀጣይ በመስክ የመረጃ በመሰብሰብና የጥራት ቁጥጥር ተግባራት ላይ የሚሳተፉ መረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ለሚያሰለጥኑ አሰልጠኞች የሚሰጠው ስልጠና በመጀመሪያው ቆጠራ ምዕራፍ ወቅት በመስክ ስራ ላይ የታዩ ክፍተቶችን በማረም ቆጠራውን በተቀመጠው የጊዜ ገደብ በተሟላ መልኩ ለማጠናቀቅ የሚያስችል ብቁ የሰው ሀይል ማዘጋጀት የሚችሉ አሰልጣኞችን የማሰልጠን ቁልፍ ተግባር መሆኑን ተገንዘባችሁ፤ ይህን ታላቅ ኃላፊነት ለመወጣት በጊዜ ወደየተመደባችሁበት የስልጠና ማዕከላት በመድረስ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው የስራ መመሪያ በመስጠት የስልጠና መድረኩን አጠቃለዋል።

የመረጃ ሰብሳቢዎችና የተቆጣጣሪዎች አሰልጠኞች ስልጠና ከጥር1/2018 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ በተዘጋጁት የስልጠና ማዕከላት መሰጠት እንደሚጀምር ከመርሀ-ግብሩ መረዳት ተችሏል።

