ሚያዚያ 22/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የስታቲስቲክስ ኖርዌይ ከምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) ጋር በመተባበር የምግብ ዋስትና ስታቲስቲክስ (Food security Statistics) መረጃ ለመተንተን የሚያስችል ስልጠና ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የቤተሰብ በጀትና ሌበር ስታቲስቲክስ ባለሙያዎች ተሰጠ።
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በርካታ መረጃዎችን በመተንተን ለተጠቃሚዎች የሚያቀርብ ሲሆን በምግብ ዋስትና ስታቲስቲክስ ላይ የሚወጣ መረጃ አለመኖሩን እንደአንድ ክፍተት በመለየት በተቋሙ ያሉ ባለሙያዎችን አቅም ለማሳደግ የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑ የቤተሰብ በጀትና ሌበር ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ፉፋ ቡልቶ ገልፀዋል።
በስልጠናው መዝጊያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ስልጠናው ብሔራዊ የተቀናጀ የቤተሰብ ጥናት እየተካሄደ ባለበት ጊዜ መሰጠቱ በቀጣይ ለሚወጣው መረጃ ትንተና የሚጠቅምና በትክክለኛው ጊዜ የተሰጠ ስልጠና መሆኑን አንስተው በስልጠናው የተሳተፉ ባለሙያዎች ያገኙትን ዕውቀት እንደመነሻ በመጠቀም በትጋት መስራት እንዳለባቸው ገልፀው ስልጠናውን ለሰጡት የስታቲስቲክስ ኖርዌይና የምስራቅና ደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (COMESA) ባለሙያዎች ምስጋናቸውን አቅርበዋል።
የስልጠናው ተሳታፊዎችም ከስልጠናው ጠቃሚ እውቅትና ልምድ እንዳገኙ ገልፀዋል።




