
የካቲት 27/2018 ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በሪከርድና ማህደር ስራ አመራርን የመዛግብት አስተዳደር ለማዘመን የሚያስችል ስልጠና ከዋናው መስሪያ ቤትና ከ26ቱ ቅርንጭፍ ጽህፈት ቤት ለተውጣጡ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።

የስልጠናውን የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የተቋሙ የሰው ሀብት አስተዳደር ስራ አስፈፃሚ አቶ አወል አባመጫ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሪፎርም የሰው ሀይል አቅም ግንባታ አንዱ ግብ መሆኑን አንስተው የሪከርድና ማህደር በዘመናዊ መልኩ ለማከናወን ስልጠናው መዘጋጀቱን ገልፀዋል። ስራ አስፈፃሚው አክለውም የስልጠናውን አስፈላጊነት ከግምት ውስጥ በማስገባት የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናውን በአግባቡ በመከታተል ለስራው የሚያስፈልገውን እውቀትና ግንዛቤ በማግኘት ወደስራችሁ ስትመለሱ ተግባር ላይ በማዋል የሪከርድና ማህደር አደረጃጀቱን ዘመናዊ ማድረግ አለባቹ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

ስልጠናው ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ቤተ መዛግብትና ቤተ መፃህፍት አገልግሎት በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች የሪከርድና ማህደር የሪከርድ ስራ አመራር ጽንሰ ሀሳብ፣ የሪከርድ አፈጣጠርና፣ አዘገጃጀትና አመዳደብ፣ የሪከርድ ዓይነቶችና ሌሎች ተያያዥ ርዕሶች ለቀጣይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።