
ህዳር 22/2018 ዓ.ም አዳማ
የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ እና ኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በጋራ የሚያካሂዱት የሲቪል ሰርቪስ ሰራተኞች ፐርሶኔል መረጃ መረጋገጥ የሙከራ ጥናት(Testing Survey) ላይ ለሚሳተፉ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

ኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ለመስክ ስራ በዘርፍ ብቃት ባላቸው የተቋሙ ባለሙያዎች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ፤ወደ ስራ ሲገባ በተግባር የበለጠ መዳበር እንዳለባቸው አንስቶ ሰልጣኞች በስልጠና ያገኙት የንድፈሃሳብናየተግባር ዕውቀትን በተገቢ መልኩ በመጠቀምየተሰጣቸውን ኃላፊነት ለመወጣት መስራት እንደሚገባቸው መልዕክት አስተላልፈዋል።

የስልጠናው መዝጊያ ፕሮግራም ላይ የተገኙት የፌዴራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር መኩሪያ ኃይሌ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለስራው ስኬት እያደረገ ለሚገኘው የተናበበ ቅድመ ዝግጅት ተግባር አመስግነው፣ ሰልጠኞች መረጃ ለሀገርና ለእየንደንዱ ሲቨል ሰርቫት ያለውን ከፍታኛ ጥቅም በመወቅ የተሰጠቸውን ኃላፊነት በትጋት መወጣት አንደሚጠበቅባቸው የስራ መመሪያ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።

