ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተቋሙ ከፍትኛ አመራሮችና ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤቢሳ አሰፋ የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት አዋጅ ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማ የሀገሪቱን መረጃ የማመንጨት ስትራቴጂና ፕሮግራሞችን ህጋዊና ወጥነት ባለው መልኩ በመምራት የሀገሪቱ የልማት ፕሮግራሞች የሚፈልጉትን የመረጃ አቅርቦት ለማሟላት ታስቦ እንደሆነ በመግለጽ የውይይት መደረኩን አስጀምረዋል።

ስለውይይት መድረኩ አስፈላጊነት በአጽንኦት የገለጹት የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ሃዋዝ የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች ለሀገራችን ጠንካራ የመረጃ አቅራቢ ተቋም ለመፍጠር የሚያችል ህጋዊ አግባብ እንዲኖረን በቀረበው ረቂቅ ሰነድ ላይ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን በማከል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ማደራጀት እንደሚጠበቅባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በውይይት መድረኩ በተዘጋጀው አዲስ አዋጅ ላይና የመንግስት መዋቅር አጠቃላይ መግቢያ እና ማብራሪያ፣ ስለአዋጁ አጠቃላይ መግለጫዎችና መመሪያ ገለጻ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።




