ሰኔ 16/2017ዓ.ም፣ ሶዶ
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት (Integrated management system (IMIS)) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ከሚገኙ 25 ሴክተሮች መስሪያ ቤቶች ለተወጣጡ ባለሙያዎች ስልጠና ሰጠ።

ተቋሙ ከተለያየ ምንጭ የሚሰበስባቸውን የስታቲስክስ መረጃዎችን በሳይንሳዊ ዘዴ በመተንተን ሪፖርቶቹን ተደራሽ ለማድረግ ጥቅም ላይ ካዋላቸው ዲጂታል የመረጃ ስርጭት መሳሪያዎች መካከል አንዱ የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርዓት (Integrated management system (IMIS) ሲሆን የስርዓቱ አጠቃቀም ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር ተጠቃሚነትን ለማሳደግ እየሰራ ይገኛል።

በዚሁ መነሻ ተቋሙ ከደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፕላንና ልማት ቢሮና ከክልሉ 25 ሴክተሮች ለተወጣጡ 100 ባለሙያዎች ስልጠና የሰጠ ሲሆን ተሳታፊዎቹ ወደ ስራ ቦታቸው ሲመለሱ ያገኙትን ልምድና ዕውቀት የመረጃ አጠቃቀም ስርዓት ተግባራዊ በማድረግ በክልሉ ለእቅድና ክትትል የስታቲስቲክስ መረጃን የመጠቀም ፍላጎትና ግንዛቤ በማሳደግ የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገልፀዋል።



