
ጥቅምት 11/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋናው መስሪያ ቤት የሪከርድና ማህደር የስራ ክፍል በአዲስ መልክ ታድሶ አገልግሎት መስጠት ጀመረ።

የሪከርድና ማህደር ክፍል ሰራተኞችለስራ ፍፁም ምቹ ያልነበረውን የስራ ክፍል ለሀገሪቱ ተመሳሳይ ተቋማት ሞዴል መሆን በሚችል ደረጃ ለሠራተኞችና በክፍሉ ለሚሰጠው አገልግሎት ምቹ ሆኖ እንዲታደስ ለሰሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

የስራ ክፍሉ ለአገልግሎት ክፍት ያደረጉት ዋና ዳይሬክተሩ ባለፉት ሶስት ዓመታት በተቋሙ ሁለንተናዊ ለውጥ ለማምጣት የተሰሩ የሪፎርም ስራዎች በተቋሙ የተልዕኮ አፈፃፀም ላይ የራሳቸውን አዎንታዊ ተፅዕኖ እየፈጠሩ እንደሆነ አንስተው በሪከርድና ማህደር የስራ ክፍል የተሰራው ደረጃውን የጠበቀ የስራ ቦታ በሁሉም የተቋሙ የስራ ክፍሎች ተደራሽ እንዲሆን በጋራ ጠንክረን መስራት አለብን ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።


