
መስከረም 12/2018 ዓ.ም
በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ሦስት ዓመታት የተሠሩት ሁሉ አቀፍ ተቋማዊ ሪፎርም ሥራዎች በክብርት ወ/ሮ ሰመሪታ ሰዋሰው የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ በተመራው የሥራ ቡድን ተጎበኘ፡፡

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ ባለፉት ሦስት ዓመታት በተቋማዊ ሪፎርም የተከናወኑ ዋና ዋና ተግባራትን የተገኙት ውጤቶች በሚመለከት ገለፃ ያቀረቡ ሲሆን የተቋማቸው አመራርና መላው ሠራተኛ ተቋሙን የዘርፉ ልህቀት ማዕከል ለማድረግ በቅንጅት እያሠሩ መሆናቸውን ገልፀዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ ጋር የነበሩት የሚኒስትር መ/ቤት ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች በተቋሙ የተከናወኑ ተግባራት ለሌሎች ተቋማት እንደ ሞዴል የሚወሰድ መሆኑን ገልፀው ተቋሙ በሀገራችን ለሚከናወኑ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊናየስነ_ህዝብ ዘርፍ ዕቅዶች፣ ፖሊሲና ስትራቴጂ ለማዘጋጀት የሚያስፈልጉት የኦፊሴላዊ መረጃ ምንጭ በመሆኑ ሚኒስትር መ/ቤታቸው የተቋሙ የመረጃ የማመንጨት አቅም የበለጠ ለማሣደግ ሁሉን አቀፍ ድጋፍ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡

ክብርት ሚኒስትሯ በአካል ተገኝተው ከጎበኙና ከቀረበላቸው ገለፃ በተቋሙ ፈጣንና ውጤታማ የሪፎርም ሥራዎች እየሠሩ እንደሆነና በተገኙት ውጤቶችም በጣም ደስተኛ መሆናቸው ገልፀው ሚኒስቴር መስሪያ ቤታቸው በቀጣይም በተቋሙ ረጅም እና አጭር ጊዜ ዕቅዶች ላይ በመመስረት የሚያደረገው ድጋፍ በተሻለ ሁኔታ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልፀዋል፡፡



