የተቋሙ የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ተደረገ

የካቲት 6/2018 ዓ.ም አርባ ምንጭ፣

631513277 891513750433848 6120258695481422350 n

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ባለፉት ስድስት ወራት ያከናወናቸው ስራ አፈፃፀም የተቋሙ ከፍተኛ አመራር፤ የዋና መስሪያ ቤትና የ26ቱ ቅ/ጽ/ቤት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት መድረክ በአርባ ምንጭ ከተማ ተገመገመ።

629741407 891513617100528 447894169077855302 n

ተቋሙ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ያከናወናቸው ተግባራት አፈፃፀም ዝርዝር ሪፖርት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ሁሴን አጎናፍር ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የተቋሙ የስድስት ወራት አጠቃላይ አፈፃፀም 90.3 በመቶ መሆኑ በቀረበው ሪፖርት ተገልጿል። በስራ አፈፃፀም የግምገማ መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ያከናወናቸው ተግባራት አፈፃፀም የተገኙትን ውጤታማ ተሞክሮዎች አጠናክረው በማስቀጠል ቀጣዩን ቀሪ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ተግባራት በተሟላ መልኩ ለማጠናቀቅ በትጋት መረባረብ እንደሚጠባቅባቸው የሥራ መመሪያ ሰጥቷል።

632363697 891513400433883 6874128896351646495 n

የተቋሙን የስድስት ወራት እቅድ አፈፃፀም ግምገማ ለማድረግ ወደ በአርባ ምንጭ ከተማ ለመጣው የተቋሙ ከፍተኛ አመራር በከተማው ኤርፖርት በጋሞ አባቶች ለተደረገላቸው አቀባበል ምስጋና አቅርበዋል።

628793867 891513440433879 2077187062245973115 n
633974313 891513423767214 8615327211062689024 n
634050639 891513807100509 8949382475816776611 n
635125058 891513540433869 6537617916611654822 n
633619793 891513557100534 6381907857816925037 n
633722359 891522787099611 1903820235957661485 n
632964116 891522887099601 5137159675427064820 n