የካቲት 7/2018 ዓ.ም አርባ ምንጭ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በአርባ ምንጭ ከተማ ያስገነባውን የአርባ ምንጭ ስታቲስቲክስ ቅ/ጽ/ቤት አዲሱን የቢሮ ህንፃ በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ እና ዶ/ር ደምሴ አድማሱ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳደር ተመረቀ።


ዶ/ር ደምሴ አድማሱ የጋሞ ዞን ዋና አስተዳደር ተቋሙ የሚያመነጫቸው የስታቲስቲክስ መረጃዎች ለሀገርና ለዞናቸው የልማት ዕድገት ያላቸውን የላቀ ፋይዳ በማስረዳት በቀጣይም ቅ/ጽ/ቤቱ በዞኑ ለሚያከናውናቸው ስራዎች ድጋፍ እንደሚያደርጉ ገልፀዋል።
በምረቃ ስነ-ስርዓቱን ላይ መልእክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋሙ በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ የተቋሙ ቅ/ጽ/ቤቶች በሂደት የራሳቸውን ለስራ ምቹ የሆኑ የቢሮ ህንፃ እንዲኖራቸው የሚያስችል ተቋማዊ የሪፎርም ስትራቴጂ ቀርፆ በትኩረት ተግባራዊ እያደረገ መሆኑን አንስተው ዛሬ በአርባ ምንጭ ከተማ የተመረቀው ቅ/ጽ/ቤቱ የቢሮ የመገልገያ ህንፃ የትኩረቱ አንድ ማሳያ መሆኑን በማስረዳት የከተማ አስተዳደሩ መሬት በማቅረብና ግንባታው በአጠረ ጊዜ እንዲጠናቀቅ ለሰጠው ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ።


የቅ/ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ አቶ ስሜ አንበሴ አዲሱ የቢሮ ህንፃ ከዚህ ቀደም የነበረባቸውን የቢሮ ክፍሎች እጥረትና ለስራ ምቹ ያለመሆን ችግርን በመቅረፍ በዕለት ተዕለት ስራቸው ላይ ከፍተኛ መነሳሳት እንደፈጠረላቸው ገልፀው የህንፃ ግንባታው እውን እንዲሆን ድጋፍ ላደረጉት አካላት በሙሉ ምስጋና አቅርበዋል።


