
ሐምሌ 30/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣
በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ተቋማዊ እውቀትን ለማጋራት የሚያስችል የዕውቀት ካፌ የማስተዋወቅ ፕሮግራም ተካሄደ።
ፕሮግራሙን በንግግር ያስጀመሩት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በተቋማዊ ሪፎርሙ ትኩረት ሰጥቶ በማከናወን ከሚገኘው ተግባራት ውስጥ አንዱ የዕውቀት አስተዳደር ስርዓትን መገንባት አገልግሎት ላይ ማዋል ሲሆን በዛሬው ዕለት የምናስተዋውቀው የዕውቀት ካፌ (knowledge cafe) አንዱ ዕውቀትን የሚጋራበት መድረክ መሆኑን በመግለጽ ሁሉም የተቋሙ ሰራተኞች በስራው ውስጥ ያገኙትን ዕውቀት በማደራጀት ለስራ ክፍሉ በመላክ የደረጀ ተቋማዊ እውቀት ግንባታ እውን እንዲሆን የበኩላቸውን እንዲወጡ መልዕክት አስተላልፈዋል።


በመድረኩ የእውቀት አስተዳደር ምንነት፣ የጥናት ስነ-ዘዴና ናሙና፣ የስታቲስቲክ መረጃ አጠቃቀምና የስርጭት አማራጮችና ሙያዊ ስነ-ምግባርን የሚመለከቱ ገለፃዎች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸው ሲሆን የመድረኩ ተሳታፊዎችም የዚህ ዓይነት መድረክ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሀሳባቸውን አጋርተዋል።







