የአርባምንጭ ዞንና ከተማ አስተዳደር ለቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱ ድጋፍ አደረጉ

የአርባምንጭ ዞንና ከተማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት አርባምንጭ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አዲሱ ቢሮ ማጠናቀቂያ የሚውሉ ድጋፍ አደረጉ።

በዞኑ እና ከተማ አስተዳደሩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት የቢሮ ውስጥ እቃ ማሟያና ለግቢ ውበት 2,400,000 ብር ግምት ያለው  በዕቃ ግዢና አስፈላጊ ግብዓቶችን በማሟላት የግቢ ማስዋብ ስራ ድጋፍ እንደዳረጉ   የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊው አቶ ስሜ አንበስ በመስክ ስራ ጉብኝት ላይ ለሚገኘው የተቋሙ ከፍተኛ አመራር የገለፁ ሲሆን የተቋሙ አመራርም ሁለቱ ተቋማት ላደረጉት ተምሳሌታዊ ተግባር ከፍተኛ ምስጋና አቅርበዋል።

የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቱን አገልግሎት ለማስጀመር ከዋናው መስሪያ ቤት በመጡት የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂና ከጠቅላላ አገልግሎት ባለሙያዎች እየተከናወነ የሚገኘው የኢንተርኔት መሰረተ ልማት ዝርጋታ ተግባራትም በአመራሩ ተጎብኝቷል።

photo 2024 12 04 18 44 41
0011