የአስተዳደራዊ መዛግብት መረጃ አሰባሰብ፣ አያያዝና ትንተና ሂደቱን ለማሻሻል የሚያግዝ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

 

1t8a1964.jpg

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከአስተዳደራዊ መዛግብት የሚገኙ መረጃዎችን እንደኦፊሴላዊ ስታቲስቲክስ መረጃ ለመጠቀም  የሚያግዝ የአቅም ግንባታ ስልጠና በአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ከተለያዩ ሴክተር መስሪያ ቤቶች ለተውጣጡ አመራሮችና  ባለሙያዎች በክልሉ ዋና ከተማ ሰመራ እየተሰጠ ይገኛል።

1t8a1930.jpg

ስልጠናው ያስጀመሩት የአፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፕላንና ልማት ቢሮ ኃላፊ ክቡር አቶ አሊ መሀመድ በክልሉ የተለያዩ ሴክተር  መስሪያ ቤቶች የሚያመነጩትን የአስተዳደራዊ መረጃዎችን አሰባሰብ፣ አያያዝ፣አደረጃጀትና ትንተና ሂደቱን በማሻሻል እንደኦፊሴላዊ  ስታቲስቲክስ መረጃ ለመጠቀም ስለመረጃዎቹ አስፈላጊነትና ያላቸው ጠቀሜታ ላይ በቂ ግንዛቤና መሠረታዊ ዕውቀት ያለው አመራርና  ባለሙያ መፍጠር ቀዳሚ ተግባር እንደሆነ አንስተው ስልጠናው ከዚህ አንፃር የሚታያውን የሰው ሀይል የአቅም ክፍተቶችን በማሻሻል  ከክልሉ የተለያዩ ሴክተር መሠሪያ ቤቶች የሚያመነጩትን የአስተዳደራዊ መረጃዎችን ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ዕቅዶች ግብዓትነት  ለመጠቀም የሚያስችል የባለሙያዎችን አቅም ለመፍጠር የተዘጋጀ ስልጠና መሆኑን አስረድተው የስልጠናው ተሳታፊዎች ወደየሴክተር  መስሪያ ቤታቸው ሲመለሱ ያገኙትን እውቀትና ልምድ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚጠባቅበቸውም መልዕክታቸውን አሰተላልፈዋል።

1t8a1985.jpg

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስታቲስቲክስ ሜቶዶሎጂና ልማት ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬከተር ክብርት ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ ስልጠናው በየሴከተሩ ያለውን የአስተዳደራዊ መረጃ አያያዝ ለማሻሻል የሚረዱ የስታቲስቲክ ፅንሰ ሀሳብና የቴክኖሎጂ አጠቀቃም ላይ በየክልሉ የሚገኙትን ባለሙያዎች አቅም በማሳደግ ከአስተዳደራዊ መዛግብት የሚገኙትን መረጃዎችን ጥራት በማሻሻል  እንደአንድ ኦፊሴላዊ ስታቲስቲክስ መረጃ ለመጠቀም በተቋሙ ሪፎርም ትኩረት ተሰጥቶ በየክልሉ እየተከናወኑ የሚገኙት ተግባራት አካል  እንደሆነ ገልፀዋል።

1t8a1934.jpg

ስልጠናው በአስተዳደር መረጃዎች አመዘጋገብ፣አያያዝና የቴክኖሎጂ አጠቀቃም ላይ ለቀጣይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥ ከስልጠናው  መርሀግብር ለመረዳት ተችሏል።

1t8a2003.jpg
1t8a2000.jpg