ነሐሴ 19/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

አምስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ሪፖርት ዝግጅት ለቴክኒክ ኮሚቴ ቀርቦ ጋር ውይይት ተደረገበት።

በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የተቋሙ የዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው ስራው በቴክኒክ ኮሚቴውና በሁሉም ባለድርሻ አካላት ድጋፍ ዛሬ ያለበት ደረጃ ላይ በመድረሱ ምስጋናቸውን በማቅረብ የውይይት መድረኩን አስጀምረዋል።

የስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ሪፖርት ዝግጅት በስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ዴስክ ሀላፊ አቶ ወርቅነህ ወ/ጊዮርጊስ ገለፃ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የቴክኒክ ኮሚቴ አባላቱ ስራው አሁን የደረሰበትን ደረጃ በቂ ግንዛቤ እንዳገኙ ገልፀዋል።

