ጥቅምት 10/2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ
የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ስራን በተቋሙ 26ቱ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ላይ ሆኖ በቅርበት ድጋፍ ለመድረግ ከዋና መስረቤት ወደ ቅርጫፍ ጽህፈት ቤት ለሚላኩ ባለሙያዎች የስራ ስምሪት ተሰጠ።

በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በመላ ሀገሪቱ 55 የስልጠና ማዕካለት ሲሰጥ የቆዬውን የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመረጃ ሰብሳቢዎች፣ የስታቲስቲሺያኖች እና የተቆጣጣሪዎች ስልጠና ለመደገፍ በየስልጠና ማዕካላቱ ተመድበው ስልጠናው በስኬት እንዲጠናቀቅ ላደረጉት ጉልህ አስተዋጽዖ ምስጋናቸውን አቅርበው የቀጣይ የመስክ ስራ ድጋፍ ስምሪት የትኩረት ማዕከሉ በቆጠራው ከመስክ የሚሰበሰበው የመረጃ ጥራት ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ ሊፈጥሩ የሚችሉ የቴክኒክ፣ የሎጅስቲክስ፣ የቴክኖሎጂ አጠቀቀምና የመረጃ ሰጪዎች ትብብር መጓደልን ችግሮችን በየቅንርጫፍ ጽህፈት ቤቶቹ ለስራው የተመደበው ሀብትና የሰው ሀይል በአግባቡ ለታለመው ስራ እንዲውል በመደገፍ እንዲሁም በየአካበቢው የሚገኙት የመንግስት አመራሮች ለስራው አስፈለጊውን ትኩረት ሰጥተው እንዲደግፉ በመረጃ ጥራት ላይ ሊፈጠሩ የሚችሉትን ማንኛውንም ችግር ቀድሞ በመፍታት የመረጃውን ጥራት ማረገጋጥ የድጋፍ ስምሪቱ ዋና አላማ መሆኑን በሚገባ ተረድተው የተሰጣቸውን ታላቅ ሀገራዊ ሀላፊነት በትጋት መፈጸም እንደሚገባቸው የስራ መመሪያና ስምሪት ሰጥተዋል።

ለቆጠራ የመስክ ስራ ድጋፍ የሚሰማራው የሰው ሀይል የቴክኒክ፣ የሎጂስቲክና ICT ቡድን በሁሉም 26 ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶች ተመድቦ፣ የተሰጠውን ሥራ በትጋት እንዲያከናውን ከዋናው መስሪያ ቤት የሥራ መመሪያ ተላልፏል።
