
ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከጥቅምት 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ እያካሄደ በሚገኘው የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመጀመሪያ ዙር የቆጠራ አፈፃፀምና የሁለተኛ ዙር ስራ ዝግጅት ላይ ከባለድርሻ አካላት ጋር በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ውይይት አደረገ።

በውይይት መድረኩ ላይ የቆጠራው የመጀመሪያ ዙር የስራ አፈፃፀም በቢዝነስ ስታቲስቲክስ ስራ አስፈፃሚ አቶ ናቃቸው ነጋሽ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ባለድርሻ አካላትም በቀረበው ሪፖርት መሰረት የቆጠራው አፈፃፀምላይ ሀሳብ፣ አስተያየትና ለቀጣይ ስራ ግብዓት የሚሆን ሀሳቦችን አንስተዋል።

በመጨረሻም የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየትና ጥያቄዎች ሰፊ የሆነ ማብራሪያና ምላሽ የሰጡ ሲሆን ከመጀመሪያ ዙር የተገኘውን ግብዓት በመውሰድ ሁለተኛ ዙር ቆጠራው በተያዘለት ጊዜ ለማጠናቀቅ እንደሚሰራ ገልፀዋል።

