ህዳር 18/2018 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ፣
በተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ለሚገኙ ሠራተኞች፣ የሃብት ማስመዝገብና ማሳወቅን በተመለከተ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠና ተሰጠ። ሥልጠናው ቀድሞ በወረቀት ሲሠራ የነበረውን የሃብት ምዝገባ ሥርዓትን ወደ ዲጂታል ሲስተም በመቀየሩ ምክንያት ሊፈጠር የሚችለውን የግንዛቤ ክፍተት ለመሙላት ታስቦ የተዘጋጀ ሥልጠና መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሥነ ምግባር መከታተያ ስራ አስፈፃሚ አቶ ዳምጠው አበራ ገለፁ። የሀብት ምዝገባ ዓላማ እና ዋና ጥቅሞች እንዲሁም የዲጂታል የሃብት ምዝገባ ሥርዓት አጠቃቀምን በተመለከተ ገለጻ ቀርቦ ግንዛቤ ተፈጥሮበታል።


