የገንዘብ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች የ22ኛውን ዓለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን አከበሩ

593367611 835880519330505 4683013276694126620 n

አዲስ አበባ፣ ኅዳር 24/2018 ዓ.ም፣

የገንዘብ፣ የፕላንና ልማት ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት ሠራተኞች ለ22ኛ ጊዜ የሚከበረውን የፀረ-ሙስና ቀን “ትውልድን በሥነ ምግባር፤ ተቋምን በአሠራር” በሚል መሪ ቃል በጋራ አከበሩ።

588401939 835879372663953 4862904725607095658 n

የሁለቱ ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት የተከብረው በዓሉ፣ ሙስና በሃገራችን አሁንም የልማት ፀር መሆኑ ታውቆ ሁሉም በየሥራ ቦታው ከሙስና የፀዳ ስራን በመስራት እና አገልግሎት በመስጠት የተጣለበትን ኃላፊነት መወጣት እንዳለበት መልዕክት ተላልፏል። የተቋማቱ ከፍተኛ አመራሮች ያላቸውን ንብራት ማሳወቂያ ቅጽ ሞልተው ርክክብ ያደረጉ ሲሆን፣ ሙስና በልማት እና በፍትሐዊነት ላይ እያደረሰ ያለውን ተጽዕኖ በሚመለከት የተዘጋጀ ጽሑፍ ቀርቦ ውይይት እና የግንዛቤ መፍጠር ስራ ተሰርተዋል።

592385762 835880189330538 6932281209073465256 n
593536241 835879805997243 2716882034586115265 n
592923943 835879899330567 7068778137783886764 n
594076561 835879779330579 4610307337694528875 n
593943501 835880142663876 6615740437782077811 n