የካቲት 11/06 2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ለሚያካሂደው የጋራ መገልገያ ዕቃዎች የዋጋ ጥናት መረጃ ሰብሳቢዎች ሥልጠና ተሰጠ።

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከመንግሥት ግዥ አገልግሎት የቀረበው የጋራ መገልገያ ዕቃዎች ዎጋ መረጃ ፍላጎት ለሟሟላት በአዲስ አበባ ከተማ በሚካሄደው የጋራ መገልገያ ዕቃዎች የዋጋ ጥናት የመስክ ስራ ላይ ለሚሳተፉ 27 ባለሙያዎች ከየካቲት 09 እስከ 13/2018 ዓ.ም በመረጃ አሰባሰብ ዘዴዎች፣ በዕቃዎች ዝርዝር መግለጫ አዘገጃጀት፣ በመረጃ አሰባሰብ ሂደት እና በመረጃ ጥራት ቁጥጥር ላይ ትኩረት አድርጎ የተሰጠ ስልጠና ነዉ ።

