
ታህሳስ 24/2018 ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የፍትሐ ብሔር ሥነ_ሥርዓትና በወንጀል ጉዳዮች ህግ ላይ ከ26ቱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ለተውጣጡ የሰው ሀብት ባለሙያዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል።

በመድረኩ ተገኝተው የስልጠናውን መክፈቻ ያደረጉት የተቋሙ የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ኃላፊ ተቋሙ በሚያከናውናቸው የሰው ሀይል ቅጥር፣ ከዋስትና ጋር የተያያዙ ጉዳዮች፣ በንብረት አያያዝ ላይ ለሚያጋጥሙ የህግ ጉዳዮች የሚያግዝ ስልጠና መሆኑን ገልፀው ፣ በዚህ ስልጠና የምትሳተፉ ባለሙያዎች የተቋሙ ሀብትና ንብረት ጠባቂ በመሆናችሁ ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል በስራ ላይ እንድታውሉ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ስልጠናው በፍትሐ ብሔር ስነ ስርዓት ህግ፣ ዓላማ፣ በወንጀል ጉዳዮች፣ በክስ አመሰራረት፣ የክስ ማመልከቻ አዘገጃጀትና ተያያዥ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ከፍትሕ ሚኒስቴር በመጡ ከፍተኛ ባለሙያዎች እየተሰጠ ይገኛል።

የስልጠናው ተሳታፊዎች የተነሱት ርዕሶች ላይ ከስራ ጋር ከሚያጋጥሟቸው ከሰው ኃይል፣ ከዋስትና ጋር ለተያያዙ ጉዳዮች ጠቃሚ መሆናቸውንና ለስራቸው ጠቃሚ ግንዛቤ እንዳገኙበት ገልፀዋል።
