የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳይ ላይ ውይይት አደረጉ

ሚያዚያ 22/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የፕላንና ልማት ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በወቅታዊ ሀገራዊ ጉዳዩች ላይ ውይይት አደረጉ።

የውይይት መድረኩ ላይ ተገኝተው መልዕክት ያስተላለፉት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋ የመንግስት ሰራተኞች የመንግስት የማድረግ አቅም በመሆናቸው በወቅታዊ ሀገራዊ የማህበራዊ፣ የኢኮኖሚያዊና ፓለቲካዊ አቅጣጫ ላይ በየጊዜው የሚደረጉት ለውጦችና ቀጣይ አቅጣጫዎች ላይ በቂ ግንዛቤ ኖሯቸው በዕውቀት ላይ ተመስርተው እንዲፈፅሙ ለማስቻል የተዘጋጀ መድረክ መሆኑን በማስረዳት ውይይቱ ላይ ሁሉም ተሳታፊዎች በነቂስ እንዲሳተፉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የመሀል ዘመን በሚል ርዕስ ለውይይቱ የተዘጋጀውን ጽሁፍ ያቀረቡት የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ረዳት ፕሮፌሰር ነብዩ ባዬ ሲሆኑ በቀረበው ገለፃ ላይ ሰፊ ውይይት የተደረገ ሲሆን በሀገራችን ወቅታዊ ሁኔታና ቀጣይ አቅጣጫ ላይ የተፈጠረልንን ግንዛቤ መነሻ በማድረግ የሚጠበቅብንን ለመወጣት እንሰራለን ሲሉ የመድረኩ ተሳታፊዎች ገልፀዋል።

1t8a7024
1t8a6952
1t8a7005
img 20250430 132434 850