የ2018ዓ.ም የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ሰራተኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

1t8a0746

መስከረም 28/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ላለፉት 25 ቀናት በመላ ሀገሪቱ በ56 የስልጠና ማዕከላት ሲሰጥ የቆየው የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመስክ ሰራተኞች ስልጠና በተሳካ ሁኔታ ተጠናቋል።

1t8a0094 1


ለስልጠናው መዝጊያ ፕሮግራም ከማዕከል በቪዲዮ መልዕክት ያስተላለፉት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በ2018 ዓ.ም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የመረጃ ሰብሳቢዎች፣ ተቆጣጣሪዎችና ስታቲስቲሺያኖች ስልጠና በታቀደው መሰረት የሚፈለገውን የዕውቀት ክህሎትና ልምድ በማስጨበጥ በተሳካ መልኩ መጠናቀቁን ገልፀው በቀጣይ በስልጠናው ያገኛችሁትን ዕውቀትና ክህሎት እንዲሁም የግል ጥረታችሁን በማከል ከእኛና ከእናንተ የሚጠበቀውን ጥራቱ የተጠበቀ የኢኮኖሚ ዘርፍ መረጃ የመሰብሰብ ሀላፊነት በአግባቡ እንዲወጡ በመግለጽ ስልጠናውን በትጋት በማጠናቀቃችሁ የእንኳን ደስ አላችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ለስልጠናው መሳካት ድጋፍ ላደረጉ የየአካባቢው አስተዳደር አካላት፣ የስልጠና ማዕከላቱ የስራ ሀላፊዎች፣ ሎጂስቲክ አቅራቢዎች፣ የሚዲያ ተቋማትና የተቋሙ ዋና መስሪያ ቤትና የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሰራተኞች ላደረጉት ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው በቀጣይም በመስክ የመረጃ መሰብሰብ ስራው በስኬት እንዲጠናቀቅ ድጋፋቸው ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

1t8a0783


በስልጠናው ከ40,000 በላይ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ወጣቶች የተሳተፉበት ሲሆን ከጥቅምት 1/2018 ዓ.ም ጀምሮ በመላ ሀገሪቱ የቆጠራው የመስክ ስራ እንደሚጀመር ተገልጿል።

1t8a0722 2
1t8a0730
1t8a0807
1t8a0827