19ኛው የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ዋና ዳይሬክተሮች ኮሚቴ ዓመታዊ ጉባኤ እየተካሄደ ይገኛል

አዲስ አበባ፣ ህዳር 24/2018 ዓ.ም፣

img 0645

19ኛው የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ዋና ዳይሬክተሮች ኮሚቴ ዓመታዊ ጉባኤ በአዲስ አበባ የአፍሪካ ኅብረት ዋና መሥሪያ ቤት እየተካሄደ ይገኛል።

img 0646
img 0662 1

በአፍሪካ ስታቲስቲክስ ዋና ዳይሬክተሮች ኮሚቴ ዓመተዊ ጉባኤ በመድረኩ ላይ የተገኙት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር አቶ ተመስገን ጥሩነህ፣ ጥራት ያለው የስታቲስቲክስ መረጃ አቅርቦት የልማት አጀንዳ ቁልፍ ጉዳይ መሆኑን በመገንዘብ፣ መንግሥታቸው በአሥር ዓመቱ ሀገር በቀል ኢኮኖሚ ልማት ዕቅድ እንደአንድቁልፍ የልማትተግባር ትኩራት ተሰጥቶት ተግባራዊ እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፣ ዛሬ 19ኛው የአህጉሪቷ የስታቲስቲክስ ዋና ዳይሬክተሮች ዓመታዊ ጉባኤን ስንጀምር፣ የውይይታችን ትኩራት የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ልማት እንደ አህጉር በአጀንዳ 2063 የተቀመጡትን ቁልፍ የልማት ግቦች ማሳለጥ በሚያስችል ደርጃ መዘመን እንዳለበት ጉባኤው ጠቃሚ ውሳኔዎችን መወሰን እንደሚገባው አቅጣጫ በመስጠት ጉባኤውን አስጀምረዋል።

img 0669 1

ስታቲስክስ፣ መረጃ ላይ ለሚመሠረት አስተዳደር የጀርባ አጥንት ነው ያሉት የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አህመድ ሽዴ፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የሚጠይቀውን የስታቲስቲክስ መረጃ ማሟላት የሚችል ዘመናዊ የስታቲስትክስ ተቋም ለመገንባት እየሠራ መሆኑን ገልጸው፣ ለሰው ኃይል ልማት ግንባታ እና የቴክኖሎጂ አቅርቦት የሚያስፈልገውን ፋይናንስ ለማቅረብ መንግሥታቸው ቁርጠኛ እና ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑን ገልጸዋል።

img 0653

የአፍሪካ ሀገራት የስታቲስቲክስ ተቋማት ዋና ዳይሬክተሮችን እንኳን በሰላም መጣችሁ፣ በማለት መልክት ያስተላለፉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ፣ የኢትዮጵያ ስቲቲስቲክስ አገልግሎት የሀገሪቷ ልማት የሚፈልገውን ጥራት ያለው መረጃ ለማቅረብ በመካከለኛ ዘመን(2016_2018 የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ዕቅድ የተቀመጡትን ቁልፍ የመረጃ ፍላጎት ለማሟላት ውጤታማ ስራዎችን እየሠራ መሆኑን አብራርተው ፣ ይህ ጉባኤ በአህጉሪቷ በዘርፉ ያሉትን ዕውቀት፣ ቴክኖሎጂ እና ልምድ የምንጋራበትን ፕላትፎርም ለመፍጠር የሚያስችል ውሳኔ እንደሚያሰተላልፍ እንደሚጠብቁ ገልጾዋል።

img 0660

በተባበሩት መንግስታት ድርጅት፣ የአፍሪካ ኢኮኖሚ ኮሚሽን የአፍሪካ ስታቲስቲክስ ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ሳሙኤል ኮቢና አኒማ፣ የአፍሪካ ስትቲስትክስ ተቋማት የአህጉሪቷ ልማት ዕቅድ እና ክትትል የሚያስፈልገውን ተዓማኒ መረጃ በቀጣይነት ለማቅረብ የሚያስችል ተቋማዊ ሪፎርም ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ገልጸው፣ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ያካሄደው ተቋማዊ ሪፎርም ለመሰል የአፍሪካ ተቋማት እንደ ሮልሞዴል የሚታይ በመሆኑ ተቋማቱ እርስ በርሳቸው ልምድ መለዋወጥ እና መማማር እንደሚጠበቅባቸው ገልፀዋል።

img 0635