ህዳር 27/2017ዓ.ም፣ የተቋሙ ከፍተኛ አመራር በወላይታ ዞን ዳሞት ሶሬ ወረዳ ዱቦ ቀበሌ በሚገኙት የቆጠራ ቦታዎች እየተካሄደ የሚገኙትን የግብርና ቆጠራ የመስክ ተግባራትን ጎበኙ።
በጉብኝቱ ወቅት ከቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊና ከመስክ ባለሙያዎች ጋር በተደረገው ውይይት እንዲሁም በተደረገ የአካል ምልከታ የመስክ ስራው በጥሩ ሁኔታ እየተካሄደ መሆኑ መገንዘብ የታቸለ ሲሆን ከአካባቢው ህብረተሰብና መረጃ ሰጪዎችም ሙሉ ድጋፍ እየተደረገላቸው መሆኑን ለመረዳት ተችሏል።
ከጉብኝት ቡድኑ ጋር በመስክ የተገኙት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሚዲያ በላሙያዎች ስለቆጠራው ለህብረተሰቡ ግንዛቤ በመፍጠር የበኩላቸውን ለመወጣት በክልል ከሚገኙት የተቋማችን የቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ሀላፊዎች ጋር እንደሚሰሩ ገልፀዋል።


