ታህሳስ 14/2017ዓ.ም፣ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እና የዓለም አቀፍ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ለሁለተኛ ጊዜ እየተካሄደ በሚገኘው የግብርና ቆጠራ ተግባራት ላይ ድጋፍ ማድረግ በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በዋናው መስሪያ ቤት ውይይት ተደረገ።
በውይይቱ ከዓለም አቀፍ የምግብና ግብርና ድርጅት (FAO) ለግብርና ቆጠራ ስራ በአማካሪነት ከተመደቡት አማካሪ ጋር በቀጣይ የሚኖሩት የቆጠራ ተግባራት ላይ ከተቋሙ ባለሙያዎች ጋር ተቀናጅቶ መስራት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ በተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር በከር ሻሌ የስራ አቅጣጫ ተሰጥቶ ውይይቱ ተጠናቋል።