የግብር ናቆጠራን በሚመለከት ከክልሉ ፕሬዝዳንት ጋር ውይይት ተደረገ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017ዓ.ም እያካሄደ በሚገኘው የግብርና ቆጠራ ላይ ከቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰን ጋር ውይይት አደረጉ።

በመድረኩ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የኢኮኖሚ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሙሉቀን ቀሬ የግብርና ቆጠራ ያለበትን አፈፃፀም ለክልሉ ፕሬዝዳንት ገልጸዋል።

የክልሉ ፕሬዝዳንት አቶ አሻድሊ ሀሰንም በበኩላቸው የግብርና ቆጠራ መረጃ ለሀገር ብሎም ለክልሉ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን በመግለፅ በክልሉ በሚያጋጥሙ ጉዳዮች ላይ ክትትልና ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።