የስርዓተ ፆታ ስታቲስቲክስ ረቂቅ መመሪያ ላይ ውይይት ተካሄደ

ሚያዚያ 22/2017 ዓ.ም፣አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስርዓተ ፆታ ስታቲስቲክስ መረጃ አሰባሰብና ጥራቱን ለማሻሻል በተዘጋጀው ረቂቅ መመሪያ ዙሪያ ከአጋር የልማት ድርጅቶች ጋር ውይይት አደረገ።

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የማህበራዊና አካቶ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈጻሚ ወ/ሮ አስናቀች ሀብታሙ ተቋሙ ወቅታዊና ተዓማኒ መረጃዎችን በጥራት ለማቅረብ የሚያስችሉ የሪፎርም ስራዎችን ተግባራዊ እያደረገ እንደሚገኝ አንስተው ዛሬ ለውይይት የቀረበውን የሀገራችን የስርዓተ ፆታ ስታቲስቲክስ ረቂቅ መመሪያ ላይ የባላድርሻ አካላትንና የአጋር የልማት ድርጅቶች አስተያየት በማካተት ተግባራዊ ለማድረግ እያተሰራ መሆኑን ገልፀው፤ በዓለም አቀፍ የሴቶች ቢሮ (UN-WOMEN) ኢትዮጵያ ቢሮ ረቂቅ መመሪያ ዝግጅት እንዲሳካ ለሰጠው ድጋፍ በማመስገን በቀጣይም ድጋፋቸው መቀጠል እንደለበት መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል ።

በዓለም አቀፍ የሴቶች ቢሮ UN-WOMEN) በኢትዮጵያ የፕሮግራም አስተባባሪ ወ/ሮ የእልፍኝ አበጋዝ በበኩላቸው ተቋማቸው በሃገሪቱ መስራት ከጀመረ ረጅም ጊዜን ያስቆጠረ ሲሆን የጾታ መረጃን በተናጠል ለማግኘት አዳጋች እንደነበር በማስታወስ የዚህ መመሪያ መዘጋጀት ከስርዓተ ጾታ መረጃዎች አቅርቦት አንጸር የነበሩ ክፍተቶችን በመሙላት ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው ገልፀዋል።

የረቂቅ መመሪያ ጽሁፍ ገለጻ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን ከተሳታፊዎች የተሰጡ አስተያየቶች እንደ ግብዓት በመውሰድ ውይይቱ ተጠናቋል።

1t8a6881
1t8a6922
1t8a6934
1t8a6911
1t8a6912