የዘጠኝ ወራት የግብርና ቆጠራ አፈፃፀም ሪፖርት ተገመገመ

ሚያዚያ 29/2017ዓ.ም አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የሁለተኛ ዙር የግብርና ቆጠራ የዘጠኝ ወራት የመስክ ስራ አፈፃፀም ለተቋሙ የግብርና ቆጠራ አስተባባሪ ኮሚቴ ቀርቦ ውይይት ተደረገ።

ለውይይቱ መነሻ የሚሆነውን የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት በግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱላዚዝ ሽፋ ቀርቦ ጥልቅ ውይይት የተደረገበት ሲሆን የእስካሁኑ የስራ አፈፃፀም በታቀደው መሰረት በጥሩ ሁኔታ እየተከናወነ እንደሚገኝ ተገምግሟል።

በመጨረሻም በስራ አፈፃፀም ሪፖርት ውይይት ላይ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ስራው አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስ መላው የተቋሙ ሰራተኛ፣ በየደረጃው ያለው አመራር፣ ስራውን በሀገር አቀፍ ደረጃ በበላይነት የሚመሩ የአብይ ኮሚቴ አባላትና በየደረጃው የሚገኙ የመንግስት አካላት ላደረጉት ያልተቋረጠ ድጋፍና ላሳዩት ትጋት ምስጋናቸውን አቅርበው ቀጣይ ቀሪ ተግባራት እስከአሁን በተጓዝንበት ቅንጅትና ትጋት ከዳር ለማድረስ መስራት እንደሚገባ የስራ አቅጣጫ በመስጠት ውይይቱ ተጠናቋል።

agri 002
agri 003
agri 001