ሙስናና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

ሚያዚያ 30/2017 ዓ.ም፣ አዲስ አበባ

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከፌደራል ሥነ-ምግባርና ፀረሙስና ኮሚሽን ጋር በመተባበር “ሙስናን በመከላከል የዜግነት ግዴታዬን እወጣለሁ’’ በሚል መሪ ቃል ሙስና እና ብልሹ አሠራርን ለመከላከል የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለተቋሙ ዋና መስሪያ ቤት ሰራተኞች እየሰጠ ይገኛል።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ሙስና ለሀገራችን ልማትና ዕድገት ፈተና ሆነው ከቀጠሉት ጉዳዮች አንዱ መሆኑን አንስተው እንደተቋም በአስተሰሰብና በድርጊት ዕለት ተዕለት በምንሰጠው አገልግሎት ላይ ከሚስተዋለው የሙስና እና ብልሹ አሠራርን ፈተና ነፃ የሆነ ተቋም ለመገንባት የሚደረገውን ጥረት ለማሳካት በግንዛቤ ላይ የተመሠረተ የሁሉንም አመራርና ሠራተኞች ተሳትፎና ቅንጅት የሚጠይቅ ቁልፍ ተግባር መሆኑን በማስረዳት፤ለቀጣይ ሁለት ቀናት የሙስና እና ብልሹ አሠራርና ባህሪያት፣ወንጀሎችና ያስከተለው ጉዳት ላይ የሚሰጠው ስልጠና ሙስናን ለመከላከል የሚደረገው ጥረት በግንዛቤ ላይ የተመሠረተ እንዲሆን ያለው ፋይደ የጎላ መሆኑን በመረዳት ተሳታፊዎች ስልጠናውን በትኩረት እንዲከታተሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

የሙስና ወንጀሎች እና ልዩ ልዩ ባህሪያት፣25ቱ የሙስና ወንጀሎች ምንነት እና በዘርፍ የሚነሱ የሙስና ጉዳዮች እና ስጋቶች ላይ ያተኮረ ስልጠና ከኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ በመጡት ዶክተር አባይ አከማቸው እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለማወቅ ተችሏል።

1t8a8089
1t8a8102
1t8a8104
1t8a8142