ግንቦት 11/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የተቋሙ ከፍተኛ አመራር በ2017በጀት ዓመት በአስተዳደር ዘርፍ በዘጠኝ ወራት የተከናወኑ ተግባራት ላይ ከሚመለከታቸው ስራ አስፈፃሚዎች ጋር የስራ ግምገማ አደረገ።

በግምገማ መድረኩ በ2017በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት በአስተዳደር ዘርፍ የተከናወኑ ተግባራት በስትራቴጂክ ጉዳዮች ስራ አስፈፃሚ አቶ ሁሴን አጎናፍር ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በመጨረሻም የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ተቋሙ በ2017 በጀት ዓመት በዘጠኝ ወራት ውስጥ የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገቡን ገልፀው በቀሩት ቀጣይ ጊዜያት መሻሻል ያለባቸው ተግባራት ላይ አቅጣጫ በመስጠት የግምገማ መድረኩ ተጠናቋል።
