ግንቦት 11/2017ዓ.ም፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎትና ኖርዌይ ስታቲስቲክስ በትብብር ለመስራት የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ በበይነ መረብ (Virtual meeting) ውይይት አደረጉ።

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2024/25ከኖርዌይ ስታቲስቲክስ ጋር በነበሩት ፕሮጀክቶች በርካታ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች የልምድ ልውውጦች መገኘታቸው ተገልጿል።

በቀጣይ በሚኖረው ፕሮጀክትም በቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ ፣ በጥናት ስነ-ዘዴ የአቅም ግንባታ ስልጠናዎች ትኩረት የሚሰጣቸው ተግባራት መሆናቸው በውይይቱ ተነስቷል።