ግንቦት 21/2017ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስታስቲክስ አገልግሎት የግብርና ቆጠራ አስመልክቶ የተቋሙ አመራሮች፣ ባለሞያዎች እና የአለም አቀፉ የምግብና እርሻ ድርጅት (FAO) ተወካዮች በአዳማና ቢሾፍቱ ዙሪያ የመስክ ጉብኝት አካሄዱ።

በመስክ ጉብኝቱ የንግድ እርሻዎች ፣ አነስተኛ ይዞታ ያላቸው የቤተሰብ እርሻ እና የእንስሳት እርባታዎች ላይ ምልከታ የተደረገ ሲሆን የግብርና ቆጠራ ስራው በጥሩ ሂደት ላይ እንደሚገኝ ከመስክ ምልከታው ለመረዳት ተችሏል።



