የሪፎርም ትግበራን በሚመለከት የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ

0001 1

ሰኔ 05/2017 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የመንግስት አገልግሎት እና የአስተዳደር ሪፎርምን አስመልክቶ ለዋናው መስሪያ ቤት ሰራተኞች  የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ተሰጠ።

ስልጠናውን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው ተቋሙ መንግስት ያስቀመጠውን የሪፎርም ትግበራ ስራ አቅጣጫ ወደተግባር ለመቀየር የሚያስችሉ በርካታ ስራዎችን በማከናወን ላይ መሆኑን ገልጸው የዛሬው ስልጠና የዚሁ አካል እንደሆነና የተቋሙ የመንግስት አገልግሎት እና የአስተዳደር ሪፎርም ትግበራ ስራዎችን አስመልክቶ የተከናወኑ ተግባራትንና ቀጣይ ስራዎችን በተመለከተ ግንዛቤ ለማስጨበጥ ታስቦ የተዘጋጀ ሲሆን ከስልጠናው በቂ  እውቀት በመያዝ ለተቋሙ የሪፎርም ስራዎች ስኬት የበኩላችሁን እንድታበረክቱ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመድረኩ በርካታ የሪፎርም ተግባራት ስራዎች አፈፃፀም በየደረጃው የቀረበ ሲሆን ከነዚህም መካከል የተቋሙ የሪፎርም ትግበራ  ደረጃዎች ዝርዝር ፣ ህግና ስርዓቶች፣አሰራርና አደረጃጀት እንዲሁም የቴክኖሎጂ አጠቃቀም እና ሌሎች ርዕሶች ዙሪያ ተቋሙ በሪፎርም  እየተገበራቸው ያሉ ስራዎችን በተቋሙ አመራሮች እና ባለሞያዎች ሰፊ ገለጻ ቀርቦ ለተነሱ ጥያቄዎች ምላሽ በመስጠት ስልጠናው  ተጠናቋል።

001 1
002 2
004 2