
ነሐሴ 7/2017ዓ.ም አዳማ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ላለፉት 10 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የግብርና ናሙና ጥናት የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።
የስልጠናው ማጠቃለያ መድረክ ላይ የተገኙት የተቋሙ የስታቲስቲክስ ዲጂታላይዜሽን ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሜሮን ክፈለው በስልጠናው ለተሳተፉ ሰልጣኞች በስልጠናው ያገኛችሁትን ዕውቀትና ክህሎት በመጠቀም በቀጣይ ለመረጃ ሰብሳቢዎች የምትሰጡትን ስልጠና በአግባቡ በማሰልጠን ጥራት ያለው መረጃ የመሰብሰብ ዕቅዱ እንዲሳካ ኃላፊነታቸውን መወጣት እንዳለባችው የስራ መመሪያ ሰጥተዋል።

በቀጣይ የመረጃ ሰብሳቢዎች ስልጠና ከነሐሴ 12−30/2017ዓ.ም እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።





