የኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ሪፖርት ዝግጅት ላይ ውይይት ተደረገ

1t8a7308

ነሐሴ 12/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣
አምስተኛ ዙር የኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ሪፖርት ዝግጅት የፕላንና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍፁም አሰፋና የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር መቅደስ ዳባ በተገኙበት ቀርቦ ውይይት ተደረገበት።

1t8a7313


በውይይት መድረኩ ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት በተቋማችን አመራሮችና ሰራተኞች፣ በመንግስትና በሌሎች ባለድርሻ አካላት ትጋትና ትብብር የመስክ ስራው በስኬት ተጠናቆ የሪፖርት ዝግጅት ተግባር እየተከናወነ እንደሆነ ገልፀዋል።

1t8a7302


በስነ-ሕዝብና ጤና ጥናት ዴስክ ሀላፊ አቶ ወርቅነህ ወ/ጊዮርጊስ የጥናቱ ሪፖርት ዝግጅት ላይ ገለፃ ቀርቦ ውይይት የተደረገበት ሲሆን አፈፃፀሙ በጥሩ ሁኔታ ላይ እንደሚገኝ ተገምግሟል።

1t8a7300