
ነሐሴ 20/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣
የፍልሰት መረጃ ለማጋራት ከዚህ ቀደም በብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት መካከል የተፈረመው መግባቢያ ሰነድ ትግበራ ላይ ለመወያየት የተዘጋጀ ወርክሾፕ በአዲስ አበባ ተጀመረ።

የኢትዮጵያ መንግስት ፍልሰትን ለማስተዳደር ብሔራዊ የፍልሰት ትብብር ጥምረት አቋቁማ በመስራት ላይ እንደምትገኝ የገለፁት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ሀገራዊ የፍልሰት የመረጃ ፍላጎትን ለማሟላት ተቋሙ በሚያከናውናቸው ናሙና ጥናቶች ውስጥ የፍልሰት መጠይቅን በማካተት ከተለያዩ ጥናቶች ጋር በማቀናጀትና ከአስተዳደራዊ መዛግብት የፍልሰት ስታቲስቲክስን ለማመንጨት እየተሰራ እንደሚገኝ በመስረዳት በዚህ ወርክ ሾፕ መግባቢያ ሰነዱን ወደ ተግባር ለማስገባት የሚያስችል አስቻይ ሁኔታዎችን መተንተን፣ ክፍተቶችን በመለየትና የመፍትሔዎችን በማመላከት የአጭር እና የረጅም የትግበራ እቅድ ማዘጋጀት ከትብብር ጥምረቱ ቡድን እንደሚጠበቅ መልዕክት አስተላልፈው፤ይህ ወርክ ሾፕ እንዲዘጋጅና እውን እንዲሆን ድጋፍ ያደረገልን እንዲሁም ሁሌም የቀጠናውን የስታቲስቲክስ መረጃ ለማሻሻል አባል ሀገራትን ለመደገፍ ያለሰለሰ ጥረት ለሚያደርገው IGAD ምስጋናቸውን አቅርበዋል።

በዚህ ውይይት ላይ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ የዓለም አቀፍ ተቋማት IOM Ethiopia, UNHCR, ILO, UN-WOMEN የፍልሰት መረጃ አስተዳደርን ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልፀዋል።



