
ነሐሴ 24/2017ዓ.ም አዲስአበባ፣
በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የአዲስ አበባ ቅ/ጽህፈት ቤት ስር ሲሰጥ የቆየው የሁለተኛ ዙር የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ።

በስልጠናው ማጠቃለያ ላይ የተገኙት በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የአዲስአበባ ቅ/ጽህፈት ቤት ስራ አስፈፃሚ አቶ ተሰማ ኡርጌሳ በስልጠና ለተሳተፋት ሰልጣኞች ስልጠናውን በሚገባ ተከታትላችሁ በማጠናቀቃችሁ እንኳን ደስ አላቹ በማለት ያላቸውን ምኞት ገልጸው በስልጠናው በቂ ዕውቀትና ልምድ እንዳገኛችሁ የሚታመን ሲሆን በቀጣይ የምታሰለጥኗቸውን መረጃ ሰብሳቢዎች ያገኛችሁትን ዕውቀትና ልምድ በተሟላ መልኩ በማስጨበጥ ለቆጠራው የመስክ ስራ ብቁ የሆኑ መረጃ ሰብሳቢዎችን በማፍራት የቆጠራው ጥራት ያለው መረጃ የመሰብሰብ ስራ እንዲሳካ ሀገራዊ ኃላፊነታቹን በትጋት እንድትወጡ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመድረኩ መረጃ ሰብሳቢዎች ከመስክ መረጃ መሰብሰብ ተግባር ወቅት ከመረጃ ሰጪዎች ጋር ማድረግ ስለሚገባቸው ተግባቦት ላይ በቫይታል ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አንተነህ ሀብቴ ሰፊ ገለጻ ቀርቦ ግንዛቤ በመፍጠርና ቀጣይ ስራ አቅጣጫ በመሰጠት የስልጠና መድረኩ ተጠናቋል።



