ለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለመስክ ስራ ፍሬሚንግ የሚያስፈልጉ አስተዳደራዊ መረጃ አቅርቦት ላይ ስልጠና ተሰጠ

1t8a9908

ጳጉሜ 1/2017ዓ.ም አዳማ፣

የኢትዮጵያ ስትቲስቲክስ አገልግሎት ከፌዴራል ፣ ከድሬዳዋ ከተማ አስተዳደርና ከሁሉም ክልል ፕላንና ልማት፣ የንግድና ገበያ ልማት ፣ ከገቢዎች፣ ከኮንስትራክሽንና ከኢንዱስትሪ ቢሮ ለተውጣጡ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች በ2018 ዓ.ም  ለሚካሄደው የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ለፍሬሚንግ ግብዓትነት የሚውሉ አስተዳደራዊ መረጃ አቅርቦት ላይ ስልጠና ተሰጠ።

1t8a9877

ስልጠናውን በንግግር ያስጀመሩት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በ2018 የኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ ከገጠር ለሚሰበሰቡት መረጃዎች ፍሬሚንግ የሚውል አስተዳደራዊ መረጃ በሚቀርብበት ሁኔታ ላይ  ግንዛቤ ለመፍጠር ታስቦ የተዘጋጀ የስልጠና መድረክ መሆኑን አንስተው የሚፈለገው መረጃ በአግባቡ ቀርቦ ለታሰበው አገልግሎት ማዋል እንዲቻል ከፌዴራል፣ ከከተማ አስተዳደርና ከሁሉም ክልል የመጣችሁ የስራ ኃላፊዎችና ባለሙያዎች ጠንካራ ተሳትፎ እንደሚያስፈልግ ገልፀው ለስራው መሳካት ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

1t8a9910

ስለኢኮኖሚ ድርጅቶች ቆጠራ የሚመለከት ገለፃ በቢዝነስ ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ ናቃቸው ነጋሽ ቀርቦ ግንዛቤ የመፍጠር ስራ የተሰራ ሲሆን ስልጠናው አስተዳደራዊ መረጃ ለመስክ ስራ ፍሬም አስፈላጊነት ላይ ለቀጣይ ሶስት ቀናት እንደሚሰጥ ከወጣው መርሀ ግብር ለመረዳት ተችሏል።

1t8a9866
1t8a9873
1t8a9892
1t8a9890