ጳጉሜ 4/2017ዓ.ም አዲስ አበባ፣
አዲሱን አመት ምክንያት በማድረግ ከሸገር ከተማ ለገጣፎ ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የባህል ቡድን በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና መስሪያ ቤት በመገኘት በጎቤና ሽኖዬ ባህላዊ ጭፈራ የእንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።

የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ወጣቶቹ የአዲስ ዓመት እንኳን አደረሳችሁ መልካም ምኞታቸውን ለመግለጽ ወደተቋማቸው በመምጣቸው የተሰማቸውን ደስታ በመግለጽ አዲሱ ዓመት የሰላም፣ የአንድነት፣ የመቻቻልና የአብሮነት ዓመት እንዲሆንላቸው መልካም ምኞታቸውን ገልፀዋል።








