
ጥቅምት 13/2018 አዲስ አበባ፣
የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የዋና መስሪያ ቤት የድጋፍ ሰጪ ሰራተኞች ተባብረው የተቋሙን ተልዕኮ ለማሳካት የበኩላቸውን እንደሚወጡ ገለፁ:: በዚሁ አጭር የጋራ መድረክ የተገኙት የተቋሙ ዋና ዳይሬክተር የሁላችንም የጋራ ግብ የመረጃ ጥራት እውን ማድረግ የሚያስችለን ርብርብ ነው ሲሉ ሰራተኞቹን አመስግነው ይህ መነሳሳት ተጠናክሮ እንዲቀጥል አደራ ብለዋል:: ሰራተኞቹም በበኩላቸው የተቋሙን አሳታፊ እና አበረታች መልካም ጅምር አመስግነዋል::

ሁሉም በየደረጃው እጅ ለእጅ ተያይዞ ጠንካራ የስታቲስቲክስ ተቋም ግንባታ እውን ለማድረግ የበለጠ እንደሚሰራ ተገልጿል::

