የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ውይይት እየተደረገ ይገኛል

ጥቅምት 21/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት ረቂቅ አዋጅ ላይ ከተቋሙ ከፍትኛ አመራሮችና  ባለሙያዎች ጋር ውይይት እያደረገ ይገኛል።

1t8a4081

የውይይት መድረኩን በንግግር የከፈቱት የተቋሙ የስራ አመራር ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤቢሳ አሰፋ የብሔራዊ ስታቲስቲክስ ስርዓት አዋጅ ያስፈለገበት ዋነኛ ዓላማ የሀገሪቱን መረጃ የማመንጨት ስትራቴጂና ፕሮግራሞችን ህጋዊና ወጥነት ባለው መልኩ በመምራት የሀገሪቱ የልማት ፕሮግራሞች የሚፈልጉትን የመረጃ አቅርቦት ለማሟላት ታስቦ እንደሆነ በመግለጽ የውይይት መደረኩን አስጀምረዋል።

1t8a4082

ስለውይይት መድረኩ አስፈላጊነት በአጽንኦት የገለጹት የዋና ዳይሬክተር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ አብነት ሃዋዝ የውይይት መድረኩ ተሳታፊዎች ለሀገራችን ጠንካራ የመረጃ አቅራቢ ተቋም ለመፍጠር የሚያችል ህጋዊ አግባብ እንዲኖረን በቀረበው ረቂቅ ሰነድ ላይ ግብዓት የሚሆኑ ሀሳቦችን በማከል የቀረበውን ረቂቅ አዋጅ ማደራጀት እንደሚጠበቅባቸው መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

1t8a4125

በውይይት መድረኩ በተዘጋጀው አዲስ አዋጅ ላይና የመንግስት መዋቅር አጠቃላይ መግቢያ እና ማብራሪያ፣ ስለአዋጁ አጠቃላይ መግለጫዎችና መመሪያ ገለጻ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት ይገኛል።

1t8a4157
1t8a4161
photo 2025 10 31 15 05 48
photo 2025 10 31 15 05 48 2