ኅዳር 11/2018 ዓ.ም
የኢትዮጵጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ከስቲስቲክስ ኖርዌይ ዓለም አቀፍ የልማት ትብብር ኃላፊ ከሆኑት ሚስ ጃነ ኡትኪለን ጋር በተቋሙ ዋና መሥሪያ ቤት ተወያዩ።
በውይይታቸው ኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት እና ስታቲስቲክስ ኖርዌይ መካከል ሲካሄድ የቆየው የአቅም ግንባታ እና የልምድ ልውውጥ ፕሮግራም እስካሁኑ ቆይታ ውጤታማ መሆኑን ተወያይቷል።
በሁለቱ ተቋማት በትብብር የሚሠሩ የአቅም ግንባታ ፕሮጀክቶች በቀጣይም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል የጋራ መግባባት ላይ ተደርሷል።