የግብርና ቆጠራ አፈፃፀም ተገመገመ

መጋቢት 12/2018 ዓ.ም አዲስ አበባ፣

a3a9651

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በ2017 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ ሲያካሂድ የነበረውን የግብርና ቆጠራ የመስክ ስራ አጠናቆ የሪፓርት እና ትንተና ሂደት አሁን የደረሰበትን ደረጃ የፕላን እና ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክብርት ዶ/ር ፍጹም አሰፋ፣ የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር አቶ አዲሱ አረጋ እና ከፍተኛ የዘርፉ ሀላፊዎች ባሉበት በዛሬው ዕለት ተገምግሟል::

a3a9679
a3a9681

ሚንስትሮቹ የቆጠራው ሂደት ውጤታማ እንደነበር በመግለፅ፤ የቆጠራውን ሪፖርትና ቀሪ ተግባራት በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ ለተጠቃሚዎች ይፋ እንዲሆን አቅጣጫ ሰጥተዋል::

a3a9662

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ ለቆጠራው ስኬታማነት ድጋፍ ላደረጉ ባለድርሻ አካላት፣ መረጃ ሰጪዎች፣ የስታቲስቲክስ ባለሙያዎች እና አመራር ብሎም በሁሉም እርከን ላይ ለሚገኙት የመንግሰት አካላት ምስጋና አቅርበው ቀሪውን የሪፖርት ተግባራት በማጠናቀቅ ለተጠቃሚዎች ይፋ እንደሚደረግ ገልፀዋል::

a3a9683