የንግድ እርሻዎች ስልጠና እየተሰጠ ይገኛል

628793867 891513440433879 2077187062245973115 n 1

መጋቢት 15/2018 ዓ.ም አዳማ፣

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የ2018 ዓ.ም የንግድ እርሻዎች እና የሌሎች ድርጅቶችና ተቋማት እርሻ ጥናት የመረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ስልጠና እየሰጠ ይገኛል።

a3a9902

በስልጠናው መክፈቻ ላይ የተገኙት የተቋሙ የስታቲስቲክስ ሜቶዶሎጂና ሲስተም ልማት ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ጀሚላ መሀመድ አሁን የሚካሄደው የንግድ እርሻዎች ጥናት በ2017 ዓ.ም ከተካሄደው ግዙፉ የግብርና ቆጠራ በተጠናቀቀበት ማግስት መሆኑን አንስተው የንግድ እርሻ ጥናቱ የ2017 ዓ.ም የግብርና ቆጠራን አጠቃላይ ጽንሰ ሃሳብና የመረጃ አሰባሰብ ስነ-ዘዴ መሰረት አድርጎ እንደሚካሄድ ገልፀዋል። ም/ዋና ዳይሬክተሯ አክለውም ለዚህ ጥናት ከመስክ መረጃ ለመሰብሰብ የምትሰማሩ መረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ስልጠናውን በትኩረት በመከታተል ጥራት ያለው መረጃ እንድትሰበስቡ ሲሉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

a3a9879

ስለጥናቱ አጠቃላይ ገለጻ ያደረጉት የግብርና ስታቲስቲክስ መሪ ስራ አስፈፃሚ አቶ አብዱላዚዝ ሽፋ የንግድ እርሻዎች ጥናት ስናካሂድ ከግብርና ቆጠራ ያገኘናቸውን ልምዶች እንደግብዓት በመጠቀም ጥራቱን የጠበቀ የንግድ እርሻዎች መረጃ ለመሰብሰብ እንሰራለን ሲሉ ገልፀዋል።

a3a9896
a3a9886
a3a9899

ስልጠናው ከ26ቱ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ለተወጣጡ 205 የሚሆኑ መረጃ ሰብሳቢዎችና ተቆጣጣሪዎች ለቀጣይ አምስት ቀናት የሚሰጥ ይሆናል።

a3a9904