የመንግስት ሰራተኞችን ፐርሶኔል መረጃ ለማረጋገጥ ሲሰጥ የቆየው የአሰልጣኞች ስልጠና ተጠናቀቀ

መጋቢት 27/2018 ዓ.ም አዳማ፣

662917515 933159106269312 5384945722805831110 n

የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር የመንግስት ሰራተኞችን መረጃ ለማረጋገጥ በስራው የሚሰማሩ መረጃ ሰብሳቢዎችን ለሚያሰለጥኑ አሰልጣኞች ሲሰጥ የቆየው ስልጠና ተጠናቀቀ።

667520192 933159036269319 7155314485053106022 n

በስልጠናው የመዝጊያ ፕሮግራም ላይ ተገኝተው የመድረኩን ማጠቃለያ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ክቡር ዶ/ር በከር ሻሌ በአሰልጣኞች ሥልጠና የተሳተፋችሁ የዩኒቨርሲቲ መምህራኖች፣ የዋናው መ/ቤትና ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ የስታቲስቲክስ ባለሙያዎች፣ ከሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን የተውጣጣችሁ ከፍተኛ ባለሙያዎች ላለፉት ሰባት ቀናት በንድፈ ሀሳብና በተግባር በወሰዳችሁት ስልጠና በቂ እውቀትና ክህሎት እንዳገኛችሁና በቂ ቅድመ ዝግጅት እንዳደረጋችሁ በመረዳት በቀጣይ የምታሰለጥኗቸው መረጃ ሰብሳቢዎች በእውቀት ላይ ተመስርተው ጥራት ያለው የመረጃ ማረጋገጥ ስራውን እንዲያከናውኑ ማሰልጠን አለባችሁ ሲሉ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል።

667409571 933158832936006 8873777866915925397 n

በመድረኩ የተገኙት የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ሽብሩ አባዲማ የመንግስት ሰራተኞችን ፐርሶኔል መረጃ የማረጋገጥ ስራ ለሀገራችን ትልቅ ትርጉም ያለው መረጃ መሆኑን በመረዳት የዛሬው መድረክም በቀጣይ ለምናከናውናቸው ስራዎች ተግባብተን የምንሄድበትና በስራው ላይ የሚያጋጥሙንን ክፍተቶች በንግግር እየፈታን በሚፈለገው ጥራትና በተያዘለት የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቅ ኃላፊነታችሁን እንድትወጡ ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

662355147 933158849602671 5811111737570512948 n

ከሰልጣኞች ለተነሱ ቴክኒካል ጥያቄዎች በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት የስነ ህዝብና ማህበራዊ ስታቲስቲክስ ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ አይናለም ተሻገርና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ም/ኮሚሽነር ክቡር አቶ ሽብሩ አባዲማ ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶበት የስልጠና መድረኩ ተጠናቋል።

661166045 933157996269423 7994369207643339027 n
661006522 933157839602772 3074908785012425220 n
662499714 933158069602749 881076668314735964 n
663141947 933157999602756 1432763928506777426 n
663134115 933158012936088 8243099666620271622 n
662591401 933158679602688 8129338979992944795 n