የስታቲስቲክስ ጥናትና ምርምር እና ስልጠና
የስታቲስቲክስ ጥናትና ምርምር እና ስልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ በኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት (ኢ.ስ.አ) በስታቲስቲክስ ሲስተም
ልማትና ሜቶዶሎጂ ዘርፍ ስር ከተዋቀሩ መሪ ስራ አስፈጻሚዎች አንዱ ሲሆን በ2016 ዓ.ም በተቋሙ የተደረገውን የመዋቅር ማሻሻያ
ተከትሎ የተመሰረተ ነው። ክፍሉ የስታቲስቲክስ ሜቶዶሎጂን በጥናትና ምርምር ማዘመን/ማሻሻል እና የስታቲስቲክስ ስልጠናዎችን
በማስተባበር ተቋማዊ አቅምን የመገንባት ሃላፊነት አለበት።
ዋና ዓላማዎች
የስታቲስቲክስ ጥናትና ምርምር እና ስልጠና መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዋና ዓላማዎች፡-
- • ከፍተኛ ጥራት ያለው የስታቲስቲክስ መረጃን ለማመንጨት ከዓለም አቀፍ ልምዶችና እና ምርጥ ተሞክሮዎች በመነሳት የስታቲስቲክስ
ሜቴዶሎጂ ጥናትና ምርምር በማካሄድ የስታቲስቲክስ ሜቴዶሎጂን ማሻሻል እና የስታቲስቲክስ ሲስተሙን ማዘመ፤ - • የስታቲስቲክስ አቅም ግንባታ ስልጠናን ማስተባበር ናቸው፡፡
ቁልፍ ተግባራት
ከዋና ዋና ተግባራት አንዱ ያሉትን የስታቲስቲክስ ናሙና ጥናቶች እና ቆጠራዎች ስነዘዴዎችን በመገምገም ለናሙና አመራረጥ፣ ለስትራቲፊኬሽን
እና ለግመታ ሂደቶች አዳዲስ ስነዘዴዎችን ማዘጋጀትና ያሉትን ማዘመን/ማሻሻል፤ የተለያዩ ሞዴሎችን እና አዳዲስ ሜቴዶሎጂዎችን በማዘጋጀት
እንዲሁም ያሉትን በማሻሻል ለዝቅተኛው የአስተዳደር እርከን/small area estimation እና የትንበያ/projection ሞዴሎችንና ቴክኒኮችን
ማዘጋጀት፣ ማስተዋወቅ፤ የስታቲስቲክስ መረጃ ጥራት እና ተነጻጻሪነትን ለማሻሻል የሚያስችሉ ስነዘዴዎች ላይ ጥናትና ምርምር ማካሄድ፤
ለአማራጭ የመረጃ ምንጮች የሚሆኑ የስታቲስቲክስ ስነዘዴዎችን በጥናትና ምርምር ማዘመን፤ እና ዓለም አቀፍ የስታቲስቲክስ ምርጥ
ተሞክሮዎችን እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን ከብሄራዊ ሁኔታ ጋር ማስማማት።
ሌላው ቁልፍ ተግባር በገጽ-ለገጽ፣ በOnline ወይም በሁለቱም ዘዴዎች ወቅታዊ የስልጠና ፍላጎት ዳሰሳን መሰረት በማድረግ የስታትስቲክስ
አቅም ግንባታ ስልጠናዎችን፣ የመማማርን እና ዕውቀት የማጋራት ባህልን ለማሳደግ የተለያዩ የስታቲስቲክስ ስልጠና ፕሮግራሞችን ማስተባበር
ነው። የስልጠና ኮርሶቹ ከonboarding/ induction (አዳዲስ ተቋሙን ለተቀላቀሉት የሚሰጥ) ጨምሮ በስታቲስቲክስ መረጃ ከዲዛይን
እስከ ስርጭት (D to D) ለሚከናወኑ ስራዎች የሚያስፈልጉ ቴክኒኮችን፣ ሜቴዶሎጂዎችን እና የተለያዩ የሶፍትዌር ክህሎቶችን፣ የዳታ ሳይንስ
እና ዘመናዊ አሰራርን፣ እንዲሁም የአመራርነት፣ የተግባቦት እና ከባለድርሻ አካላት ጋር በሚኖረን መስተጋብር ላይ የሚያስፈልጉ ልል ክህሎት
(Soft Skill) ያካትታሉ። የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት በስታቲስቲክስ ምርምር እና ስልጠና የልህቀት ማዕከል ለመመስረት አልሟል።
መዋቅር (አደረጃጀት)
መሪ ሥራ አስፈፃሚው ተግባሩን እና ኃላፊነቱን በብቃት ለመወጣት በሁለት ዴስኮች ተደራጅቷል። እነዚህም፡-
- • የስታቲስቲክስ ጥናትና ምርምር ዴስክ
- • የስታቲስቲክስ ስልጠና ማስተባበሪያ ዴስክ ናቸው፡፡
ውጤቶች
- • አዳዲስ የስታቲስቲክስ ሥነ-ዘዴዎች
- • የስታቲስቲክስ ሞዴሎች፣ ማዕቀፎች እና መሳሪያዎች
- • በጥናት ንድፍ፣ በናሙና፣ በትንበያ እና በዳታ ሳይንስ ስነዘዴዎች ላይ የሚደረግ የምርምር ጤት/ፈጠራ
- • የተቋማዊ ስታቲስቲክስ አቅም መገንባት
- • የተሻሻለ የመማማር ባህል እና የእውቀት ሽግግር
- • የስልጠና መመሪያዎች እና የመማሪያ ቁሳቁሶች
- • ከሌሎች ተቋማት ጋር የሚደረግ የሥራ ግንኙነት እና ትብብር
- • የስልጠና ስርአተ-ትምህርት (Training Curriculum)
- • የብቃት ማረጋገጫ / ሰርተፍኬት (Certification)